የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም፡ የአዲሱ እመ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ግንባታ
ጣና ሐይቅ ዳርቻ ላይ የሚገኘው ታሪካዊው ደብር ቅዱስ ማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም፣ የብዙ መነኮሳትና የምዕመናን መንፈሳዊ ማዕከል ነው። ይሁን እንጂ፣ ለረጅም ዘመናት ለገዳሙ ክብረ በዓላት፣ ለሱባኤና ለጸበል የሚመጡ በርካታ እናቶችና እህቶች ከግዝት በር አልፈው ወደ ዋናው ቤተክርስቲያን መግባትና ማስቀደስ አይችሉም ነበር።
ለእነዚህ ምዕመናን አገልግሎት የሚውል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታቦት ያለበት መቃኞ ቢኖርም፣ በዓለ ንግሥ ሲሆን ቅዳሴው የሚከናወነው በተተከሉ ድንኳኖች ውስጥ ነበር። ይህ ደግሞ፡-
- ለቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ መፈተት ተገቢ አይደለም።
- ለመናንያን መንፈሳዊ ሕይወትም ከባድ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።
የታሪክና የትውፊት ውርስ
በዚህ ምክንያት፣ ታላቁ ማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም፣ የብዙ ምዕመናንን ልመና በመቀበል፣ ለገዳሙ ታሪካዊ ክብር የሚመጥን እና የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት የጠበቀ ውብ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (እመ ቅዱሳን) ቤተ ክርስቲያን በመገንባት ላይ ይገኛል።
ይህ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ለዓመታት የዘለቀውን የመንፈሳዊ አገልግሎት ክፍተት የሚሞላ ሲሆን፣ የእመቤታችን በረከት ለትውልድ የሚተላለፍበት የተቀደሰ መካነ ቅድሳት ይሆናል።



